ትንቢተ ሚክያስ 7
7
የሕዝቡ ሁሉ ምግባረ ብልሹነት
1የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።
2ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቶአል፥ በሰው መካከል ቅን የለም፤ ሁሉም ለደም ያደባሉ፥ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።
3እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
4ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።
5በጓደኛ አትታመኑ፥ በወዳጅም አትተማመኑ፤ የአፍህን ደጅ በጉያህ ከምትተኛው ጠብቅ።
6 #
ማቴ. 10፥35፤36፤ ሉቃ. 12፥53። ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፥ ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፥ ምራት በአማትዋ ላይ ትነሣለችና፤ የሰው ጠላቶች የቤቱ ሰዎች ናቸው።
7እኔ ግን ወደ ጌታ እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።
ንስሐና በእግዚአብሔር መታመን
8ጠላቴ ሆይ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ብወድቅ እነሣለሁና፤ በጨለማ ብቀመጥ ጌታ ብርሃኔ ነውና።
9በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ።
10ጠላቴም ታያለች፥ “ጌታ አምላክህ የት ነው?” ያለችኝን ኀፍረት ይከድናታል፥ ዐይኖቼ ያዩአታል፤ አሁን እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።
የመታደስ ትንቢት
11ቅጥርሽ የሚሠራበት ቀን፥ በዚያ ቀን ድንበርሽ ይስፋፋል።
12በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብጽ ከተሞች፥ ከግብጽ እስከ ወንዙ፥ ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከተራራ እስከ ተራራ ድረስ ወደ አንተ ይመጣሉ።
13ምድሪቱ ግን በሚኖሩባት ከሥራቸው ፍሬ የተነሣ ባድማ ትሆናለች።
14በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
15ከግብጽ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳየዋለሁ።
16አሕዛብ ያያሉ፥ በኀይላቸው ሁሉ ያፍራሉ፤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮዎቻቸውም ይደነቁራሉ።
17እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፥ በምድር እንደሚሳቡ ፍጥረታት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጋቸው ይመጣሉ፤ በፍርሃት ወደ ጌታ አምላካችን ይመጣሉ፥ ከአንተ የተነሣ ይፈራሉ።
የእግዚአብሔር ርኅራኄና ፅኑ ፍቅር
18በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።
19እንደገና ይራራልናል፤ በደሎቻችንን ይረጋግጣል፥ ኃጢአታቸውን ሁሉ በባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ።
20ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን እንደማልህላቸው እውነትን ለያዕቆብ፥ ርኅራኄን ለአብርሃም ታደርጋለህ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሚክያስ 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ