የማቴዎስ ወንጌል 8:14-17

የማቴዎስ ወንጌል 8:14-17 መቅካእኤ

ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ አማቱ በትኩሳት ታማ ተኝታ አያት፤ እጅዋን ዳሰሳት፤ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለችው። በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ መናፍስቶቹን ሁሉ በቃል አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ፤” የተባለው እንዲፈጸም ነው።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች