ኦሪት ዘሌዋውያን 15
15
ከሰውነት ውስጥ ስለ ሚወጡ ፈሳሾች
1ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 2#ዘኍ. 5፥2።“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ ማንም ሰው ከሰውነቱ ውስጥ ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፥ ከእርሱ የሚወጣው ፈሳሽ ርኩስ ነው። 3ከእርሱ የሚፈስሰው ነገር ርኩስነቱ ይህ ነው፤ ፈሳሹ ነገር ከሰውነቱ ቢፈስስ ወይም ከመፍሰሱ ቢቆም፥ ለእርሱ ርኩስ ይሆናል። 4ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚተኛበት መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል። 5መኝታውንም የሚነካ ማንም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 6ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው በተቀመጠበት በማናቸውም ነገር ላይ የሚቀመጥበት ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 7ፈሳሽ ነገር ያለበትን ሰው ገላውን የሚነካ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 8ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው በንጹሕ ሰው ላይ ቢተፋ፥ የተተፋበት ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 9ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። 10#ዘሌ. 11፥24-25፤27-28፤39-40፤ 14፥46-47።እርሱም ከተቀመጠበት በታች ያለውን ማናቸውንም ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 11ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው እጁን በውኃ ሳይታጠብ ማንንም ሰው ቢነካ፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 12ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይሰብሩታል፤ የእንጨቱም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይታጠባል።
13 #
ዘሌ. 14፥8። “ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ፥ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፥ እርሱም ንጹሕ ይሆናል። 14#ዘሌ. 12፥8፤ 14፥22።በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዞ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በጌታ ፊት ይመጣል፥ ለካህኑም ይሰጣቸዋል። 15ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።
16 #
ዘፀ. 19፥15፤ ዘዳ. 23፥11-12፤ 1ሳሙ. 21፥6። “ማንም ሰው ዘሩ ከእርሱ ብልት ቢፈስስ፥ ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 17ዘሩ የነካው ልብስ ሁሉ ቆዳም ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 18ወንዱ ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ ዘሩን ቢያፈስስ፥ ሁለቱ በውኃ ይታጠባሉ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩሶች ይሆናሉ።
19 #
ዘሌ. 12፥2፤ 5፤ 2ሳሙ. 11፥4፤ ሕዝ. 36፥17። “ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት ከሰውነቷም ውስጥ የሚፈስሰው ነገር ደም ቢሆን፥ በወር አበባዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 20በወር አበባዋ ጊዜ የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል። 21መኝታዋንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 22የምትቀመጥበትንም ነገር ሁሉ የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 23በመኝታም ወይም በማናቸውም ነገር ላይ ብትቀመጥ፥ እርሱ በሚነካው ጊዜ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 24#ዘሌ. 18፥19፤ 20፥18፤ ሕዝ. 18፥6።ማንም ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ የወር አበባዋ ቢነካው፥ እርሱ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።
25 #
ማቴ. 9፥20-22፤ ማር. 5፥25-34፤ ሉቃ. 8፥43-48። “አንዲትም ሴት ከወር አበባዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከወር አበባዋ ጊዜያት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ ፈሳሹ ነገር በሚፈስስበት ቀን ሁሉ በርኩስነትዋ ትቀጥላለች፤ በወር አበባዋ ጊዜያት እንደ ሆነች እንዲሁ እርሷ ርኩስ ትሆናለች። 26ፈሳሹም ነገር በሚፈስስበት ጊዜያት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በወር አበባዋ ጊዜ እንደነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ እንደ ወር አበባዋ ርኩስነት ርኩስ ይሆናል። 27እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 28#ዘሌ. 15፥13-15።ከፈሳሽዋም ብትነጻ ሰባት ቀን ትቈጥራለች፥ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ትሆናለች። 29በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዛ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመጣቸዋለች። 30ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ስለ ፈሳሽዋም ርኩስነት ካህኑ በጌታ ፊት ያስተሰርይላታል።
31 #
ዘሌ. 5፥2-3፤ 22፥9፤ ዘኍ. 19፥13፤ 20። “እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”
32ፈሳሽ ነገር ላለበት ሰው፥ ዘሩም ለሚፈስስበት በእርሱም ምክንያት ለሚረክሰው ሰው ሕጉ ይህ ነው፤ 33እንዲሁም በወር አበባዋም ለታመመች፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ የረከሰችንም ሴት ለሚገናኝ ሰው ሕጉ ይህ ነው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 15: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ