መጽሐፈ ኢያሱ 9:1-2

መጽሐፈ ኢያሱ 9:1-2 መቅካእኤ

እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በቈላማውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም፥ ይህን በሰሙ ጊዜ፥ ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።