መጽሐፈ ኢዮብ 8
8
1ሹሐዊውም ቢልዳድ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“እስከ መቼ ይህን ትናገራለህ?
የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናል?
3በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን?
ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
4ልጆችህ በድለውት እንደሆነ፥
እርሱ በበደላቸው እጅ ጥሎአቸዋል።
5እግዚአብሔርን ብትሻ፥
ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትማጸን፥
6ንጹሕና ቅን ብትሆን፥
በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥
የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል።
7ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ
ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።”
8 #
ሲራ. 8፥9። “እንግዲህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥
አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትኩረት ስጥ፥
9እኛ የትናንት ብቻ ነን፥ ምንም አናውቅም፤
ቀኖቻችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ናቸውና።
10እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥
ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?”
11“በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን?
ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
12ገና ሲለመልም ሳይቀጠፍም፥
ከአትክልት ሁሉ በፊት ይደርቃል።
13እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፥
የአምላክ አልባ ሰውም ተስፋ ይጠፋል።
14ተስፋው ይቈረጣል፥
መተማመኛው እንደ ሸረሪት ቤት ይሆናል።
15ቤቱን ይደገፈዋል፥ ነገር ግን አይቆምለትም፥
ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።
16ከፀሐይም ትኩሳት በፊት እርጥብ ነው፥
ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል።
17በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፥
የድንጋዩቹን ቦታ ይመለከታል#8፥17 “በድንጋዮች መካከል ይኖራል” የሚለውን ትርጒም የሚሰጡም አሉ።።
18ከቦታው ቢጠፋ፦
አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።
19እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፥
ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።”
20“እነሆ፥ እግዚአብሔር ፍጹሙን ሰው አይጥለውም፥
የክፉዎችን እጅ አያበረታም።
21አፍህን እንደገና በሳቅ፥
ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላዋል።
22የሚጠሉህ ኃፍረት ይከናነባሉ፥
የክፉዎችም ድንኳን አይገኝም።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ