መጽሐፈ ኢዮብ 7
7
1“የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?
ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?
2አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥
ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥
3እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥
የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ።
4በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ።
ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥
እስኪ ነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ።
5ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥
ቆዳዬ ያፈከፍካል እንደገናም ይመግላል።
6ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥
ያለ ተስፋም ያልቃሉ።”
7“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥
ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።
8የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፥
ዓይንህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔም አልገኝም።
9 #
ጥበ. 2፥1-4። ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥
እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም።
10ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥
ስፍራውም ዳግመኛ አያውቀውም።”
11“ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥
በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥
በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።
12እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ዓሣ አንበሪ?
ባላዬ ጠባቂ የምታኖርብኝ?#7፥12 ኢዮብ እግዚአብሔርን ምንም የሚያሰጋው ነገር እንደሌለ እየገለጸ ነው።
13እኔም፦ አልጋዬ ያጽናናኛል፥
መኝታዬም የኀዘን እንጉርጉሮዬን ያቀልልኛል ባልሁ ጊዜ፥
14አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥
በራእይም ታስደነግጠኛለህ፥
15ከዚህ ሥጋ ይልቅ
ነፍሴ መታነቅንና ሞትን መረጠች።
16ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥
ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።
17 #
መዝ. 8፥4፤ 143፥3። ሰው ምንድነው ታከብረው ዘንድ፥#7፥17 ይህንን የሚመስል ጥያቄ በመዝ 8፥ 5 ላይም ይገኛል። ሆኖም በመዝሙሩ የተገለጸው አድናቆትና መገረም ሲሆን፥ በኢዮብ በኩል ግን እግዚአብሔር ስለ ሰው ከሚያስብ ትኩረቱን ወድ ሌላ ቢያዞር ይሻላል የሚል ነው።
ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥
18ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥
ሁልጊዜስ ትፈታተነው ዘንድ?
19የማትተወኝ እስከ መቼ ነው?
ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
20ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ?
ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ?
ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?
21ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም?
ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም?
አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥
ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ኢዮብ 7
7
1“የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?
ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?
2አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥
ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥
3እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥
የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ።
4በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ።
ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥
እስኪ ነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ።
5ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥
ቆዳዬ ያፈከፍካል እንደገናም ይመግላል።
6ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥
ያለ ተስፋም ያልቃሉ።”
7“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥
ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።
8የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፥
ዓይንህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔም አልገኝም።
9 #
ጥበ. 2፥1-4። ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥
እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም።
10ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥
ስፍራውም ዳግመኛ አያውቀውም።”
11“ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥
በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥
በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።
12እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ዓሣ አንበሪ?
ባላዬ ጠባቂ የምታኖርብኝ?#7፥12 ኢዮብ እግዚአብሔርን ምንም የሚያሰጋው ነገር እንደሌለ እየገለጸ ነው።
13እኔም፦ አልጋዬ ያጽናናኛል፥
መኝታዬም የኀዘን እንጉርጉሮዬን ያቀልልኛል ባልሁ ጊዜ፥
14አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥
በራእይም ታስደነግጠኛለህ፥
15ከዚህ ሥጋ ይልቅ
ነፍሴ መታነቅንና ሞትን መረጠች።
16ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥
ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።
17 #
መዝ. 8፥4፤ 143፥3። ሰው ምንድነው ታከብረው ዘንድ፥#7፥17 ይህንን የሚመስል ጥያቄ በመዝ 8፥ 5 ላይም ይገኛል። ሆኖም በመዝሙሩ የተገለጸው አድናቆትና መገረም ሲሆን፥ በኢዮብ በኩል ግን እግዚአብሔር ስለ ሰው ከሚያስብ ትኩረቱን ወድ ሌላ ቢያዞር ይሻላል የሚል ነው።
ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥
18ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥
ሁልጊዜስ ትፈታተነው ዘንድ?
19የማትተወኝ እስከ መቼ ነው?
ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
20ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ?
ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ?
ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?
21ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም?
ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም?
አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥
ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”