መጽሐፈ ኢዮብ 35
35
1ኤሊሁም ደግሞ ቀጠለ፤ እንዲህም አለ፦
2“ይህ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህን?
ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን?
3አንተ፦ ምን ትጠቀማለህ?
ኃጢአት ባልሠራስ ምን እጠቀማለሁ? ብለህ ጠይቀሃልና።#35፥3 ኤሊሁ ኢይብን እየወቀሰው ነው፤ ኃጢአት መሥራት ወይንም አለመሥራት በእግዚአብሔር ፊት ምንም ልዩነት የለውም እያልክ ነው የሚል ወቀሳ ይሠነዝራል።
4እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉትም ባልንጀሮችህ እመልሳለሁ።
5ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፥
ከአንተም በላይ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት።
6 #
ኢዮብ 22፥2፤3። ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ?
መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ?
7ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ?
ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?
8ክፋትህ እንደ አንተ ያለውን ሰው ይጐዳዋል፥
ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።
9ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፥
ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጣራሉ።
10-11ነገር ግን፦ በሌሊት የደስታ መዝሙሮችን የሚለግስ፥
ከምድርም እንስሶች ይልቅ የሚያስተምረን
ከሰማይም ወፎች ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን
ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም።
12በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥
እርሱ ግን አይመልስላቸውም።
13በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥
ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፥
14እንዲያውም፦ ‘አላየውም፥
ጉዳዩ በእርሱ ፊት ነው፥ እኔም አጠብቀዋለሁ’ ስትልማ የባሰ ነው።
15አሁን ግን በቁጣው ስላልቀጣ፦
ትዕቢት ምን እንደሆነ የማያውቅ መሰለህ?
16ስለዚህ ኢዮብ ከንቱ ንግግርን ከአፉ ያወጣል፥
ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 35: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ