መጽሐፈ ኢዮብ 30
30
1“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥
አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥
በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።
2የቀድሞ ጥንካሬአቸው ጠፍቶ ነበርና
የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይጠቅማል?
3በችግርና በራብ መንምነው፥
በፈረሰውንና በተተወው የጨለመ
ምድረ በዳን ሥራ ሥሮችን ያኝካሉ።
4በቁጥቋጦ አጠገብ ያለውን
ጨው ጨው የሚለውን ቅጠላ ቅጠል ይቀጥፋሉ፥
እንዲሞቃቸውም የክትክታ ሥር ይበላሉ።
5ከሰዎች ተለይተው ተሰደዱ፥
በሌባ ላይ እንደሚጮኽ ይጮኹባቸዋል።
6በሸለቆ ጉድጓድ፥ በምድርና
በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ።
7በጫካ ውስጥ ይጮኻሉ፥
ከቁጥቋጦ በታች ተሰብስበዋል።
8የአላዋቂና የነውረኞች ልጆች ናቸው፥
ከምድርም በግርፋት የተባረሩ ናቸው።”
9“አሁንም እኔ መዝፈኛና መተረቻ ሆንኋቸው።
10ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ራቁ፥
አክታቸውንም በፊቴ መትፋትን አልተዉም።
11የቀስቴን አውታር አላልቶብኛል፥ አዋርዶኝማል፥
እነርሱም በፊቴ ልጓማቸውን ፈትተዋል#30፥11 ሊያጠቁኝ።።
12በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥
እግሬንም ያሰናክላሉ፥
የጥፋታቸውን መንገዶች በእኔ ላይ ይቀይሳሉ።
13ጐዳናዬን ያበላሻሉ፥
ረዳት የሌላቸው#30፥13 ወይም የማያስፈልጋቸው። ሰዎች መከራዬን ያበዛሉ።
14በሰፊው መከላከያን ጥሰው እንደሚመጡ ይመጡብኛል፥
በፍርስራሽ ውስጥ ይንከባለላሉ።
15ድንጋጤ በላዬ ተመለሰብኝ፥
ክብሬንም እንደ ነፋስ ያሳድዱታል፥
ብልጽግናዬም እንደ ደመና አልፋለች።”
16“እነሆ ሕይወቴ እያለቀች ነው፥
የመከራም ዘመን ያዘኝ።
17የሌሊቱ ስቃይ እስከ አጥንቶቼ ድረስ ይዘልቃል፥
ሁለመናዬንም ስለሚበላኝ ጅማቶቼ አያርፉም።
18ከሕመሜ ብርታት የተነሣ ልብሴ#30፥18 ቆዳዬ ተበላሸ ማለትም ይሆናል። ተበላሸ፥
እንደ ቀሚስ ክሳድ ያንቀኛል።
19በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥
አፈርና አመድም መሰልሁ።
20ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፥
ተነሣሁ፥ ነገር ግን ዝም ብለህ ተመለከትኸኝ።
21ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፥
በጠንካራ እጅህም አሰቃየኸኝ።
22በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስጋለብከኝ፥
በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ።
23ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።”
24“ነገር ግን ሰው በወደቀ ጊዜ እጅ አይዘረጋምን?#30፥24 “እርዱኝ ለማለት” ወይንም በተደራጊ ከተነበበ፥ “ለመርዳት ፈቃደኛ አይደለምን?”
በጥፋቱስ ጊዜ አይጮኽምን?
25ለተጨነቁት አላለቀስሁምን?
ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን?
26ነገር ግን በጎነትን ስጠባበቅ ክፉ ነገር መጣብኝ፥
ብርሃንን ተስፋ ሳደርግ ጨለማ መጣ።
27አንጀቴ ተናወጠ፥ አላረፈምም፥
የመከራም ዘመን መጣብኝ።
28በፀሐይ ሳይሆን በትካዜ ጠቁሬ ሄድሁ፥
በጉባኤም መካከል ቆሜ ጮኽሁ።
29ለቀበሮ ወንድም፥
ለሰጐንም ባልንጀራ ሆንሁ።
30ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥
አጥንቴም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠለ።
31ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥
እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ መሳርያ ሆነ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 30: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ