መጽሐፈ ኢዮብ 28
28
1“በእውነቱ ብር የሚወጣበት፥
ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
2ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥
ከቀለጠ ድንጋይም መዳብ ይወጣል።
3ለጨለማ ወሰን ይደረጋል፥ #28፥3 የማዕድን ፈላጊዎች ከመሬት በታች የሚሠሩትን ያመለክታል።
የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ጫፍ ድረስ ይፈላልጋል።
4ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ
በመንገድኞችም ተረስተዋል፥#28፥4 መንገደኞች ከመሬት ሥር የሚከናወነውን ሥራ አያዩም፤ ቦታውም እሩቅ ስለሆነ ቆፋሪዎችን የሚያስታውስ የለም።
ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ።
5ምድር እንጀራን ታበቅላለች፥
ከበታቿ ያለው ግን እንደ እሳት ይገለባበጣል።
6እዚያ ድንጋዮችዋ የሰንፔር መከማቻ ናቸው፥
የወርቅም ድቃቂ ይገኛል።”
7“መንገድዋን ጭልፊት አያውቀውም፥
የአሞራም ዐይን አላየውም።
8ኩሩ አውሬዎች አልረገጡአትም፥
ደቦል አንበሳ አላለፈባትም።”
9“ሰው ወደ ጠንካራ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥
ተራራውንም ከመሠረቱ ይገለብጣል።
10ከድንጋይ ውስጥ መተላለፍያ ይሠራል፥
ዓይኑም ዕንቁን ሁሉ ታያለች።
11የወንዞችን መነሻዎች ይፈልጋል#28፥11 የውሆችን መነሻ የሚፈልገው ለመገደብና የማዕድን ቁፈራውን ለማከናወን ነው።፥
የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።”
12 #
መክ. 7፥24-25፤ ሲራ. 1፥6፤ ባሮክ 3፥14-15፤29-33። “ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው?
የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
13ሰው መንገድዋን አያውቅም፥
በሕያዋን አገር አትገኝም።
14ቀላይ፦ በእኔ ውስጥ የለችም ይላል፥
ባሕርም፦ በእኔ ዘንድ የለችም ይላል።
15 #
ምሳ. 3፥14፤ 8፥10-11፤19፤ 16፥16፤ ጥበ. 7፥7-11። በንጹሕ ወርቅ አትገኝም፥
ዋጋዋም በብር አይተመንም።
16በኦፊር ወርቅ፥
በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
17ወርቅና ብርጭቆ አይወዳደሩአትም፥
ከጥሩ ወርቅ በተሠራ ዕቃም አትለወጥም።
18ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም።
የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቁ ይልቅ ይበልጣል።
19የኢትዮጵያ ቶጳዝዩን#28፥19 የከበረ ድንጋይ። አይተካከላትም፥
በንጹሕ ወርቅም አትገመትም።”
20“እንግዲያውስ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች?
የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
21ከሕያዋን ሁሉ ዐይን ተሰውራለች፥
ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።
22ጥፋትና ሞት፦ ስለ እርሷ በወሬ ሰማን ብለዋል።”
23 #
ምሳ. 8፥22-31። “እግዚአብሔር መንገድዋን ያስተውላል፥
እርሱም ስፍራዋን ያውቃል።#ምሳ. 2፥6፤ ሲራ. 1፥1፤ ያዕ. 1፥5።
24እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥
ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
25ለነፋስ ሚዛንን ባደረገለት ጊዜ፥
ውኆችንም በስፍር በሰፈረ ጊዜ፥
26 #
ኢዮብ 38፥25፤ ምሳ. 3፥20። ለዝናብም ሥርዓትን፥
ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥
27በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፥
አዘጋጃትም፥ ደግሞም መረመራት።
28 #
መዝ. 111፥10፤ ምሳ. 1፥7፤ 9፥10፤ ሲራ. 1፥13-21። ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥
ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 28: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ