መጽሐፈ ኢዮብ 27
27
1ኢዮብም ምሳሌውን ቀጠለ፥ እንዲህም አለ፦
2“ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን!
ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!
3እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥
4ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥
አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም።
5እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥
እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም።
6በጽድቄ እጸናለሁ እርሱንም አልተውም፥
ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱም እንኳን ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።”
7“ጠላቴ እንደ በደለኛ፥
በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
8እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥
አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው?
9በውኑ መከራ በመጣበት ጊዜ፥
እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
10ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?
እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
11እኔ ስለ እግዚአብሔር ሥራዎች#27፥11 ቃል በቃል እጅ። አስተምራችኋለሁ፥
ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም።
12እነሆ፥ ሁላችሁም አይታችኋል፥
ታዲያ ለምን በከንቱ ትባክናላችሁ?”
13“እነሆ የበደለኛ እድል ፈንታ ከእግዚአብሔር ዘንድ፥
ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ይህችው፥
14ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይሞታሉ፥
ዘሩም በቂ እንጀራ ከቶ አያገኝም።
15ለእርሱ የተረፉትም በቸነፈር ይቀበራሉ፥
መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
16እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥
ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥
17እርሱ ያዘጋጀው ይሆናል፥ ነገር ግን ጻድቅ ይለብሰዋል፥
ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል።
18የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፥
ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው።
19ባለ ጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው፥
ዓይኑን ሲከፍት፥ እርሱም የለም#27፥19 ሀብቱ፥ ቤቱ ወይም ሕይወቱ ጠፍቶአል ለማለት ይቻላል።።
20ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥
በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።
21የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፥
ከቦታውም ይጠርገዋል።
22ነፋሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፥
እርሱ ግን ከእጁ ፈጥኖ ለመሸሽ ይታገላል።
23ነፋሱ ያጨበጭብበታል፥
ከስፍራውም በፉጨት ያስወጣዋል።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 27: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ኢዮብ 27
27
1ኢዮብም ምሳሌውን ቀጠለ፥ እንዲህም አለ፦
2“ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን!
ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!
3እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥
4ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥
አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም።
5እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥
እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም።
6በጽድቄ እጸናለሁ እርሱንም አልተውም፥
ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱም እንኳን ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።”
7“ጠላቴ እንደ በደለኛ፥
በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
8እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥
አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው?
9በውኑ መከራ በመጣበት ጊዜ፥
እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
10ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?
እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
11እኔ ስለ እግዚአብሔር ሥራዎች#27፥11 ቃል በቃል እጅ። አስተምራችኋለሁ፥
ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም።
12እነሆ፥ ሁላችሁም አይታችኋል፥
ታዲያ ለምን በከንቱ ትባክናላችሁ?”
13“እነሆ የበደለኛ እድል ፈንታ ከእግዚአብሔር ዘንድ፥
ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ይህችው፥
14ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይሞታሉ፥
ዘሩም በቂ እንጀራ ከቶ አያገኝም።
15ለእርሱ የተረፉትም በቸነፈር ይቀበራሉ፥
መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
16እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥
ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥
17እርሱ ያዘጋጀው ይሆናል፥ ነገር ግን ጻድቅ ይለብሰዋል፥
ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል።
18የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፥
ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው።
19ባለ ጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው፥
ዓይኑን ሲከፍት፥ እርሱም የለም#27፥19 ሀብቱ፥ ቤቱ ወይም ሕይወቱ ጠፍቶአል ለማለት ይቻላል።።
20ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥
በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።
21የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፥
ከቦታውም ይጠርገዋል።
22ነፋሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፥
እርሱ ግን ከእጁ ፈጥኖ ለመሸሽ ይታገላል።
23ነፋሱ ያጨበጭብበታል፥
ከስፍራውም በፉጨት ያስወጣዋል።”