መጽሐፈ ዮዲት 3

3
1ስለዚህ ሰላምን የሚለምኑ መልዕክተኞችን እንዲህ በማለት ላኩበት፦ 2“እነሆ፥ እኛ የታላቁ ንጉሥ የናቡከደነፆር አገልጋዮች በፊትህ እጅ እንነሣለን፥ በፊትህ እንደ ወደድህ አድርገን። 3እነሆ መኖሪያዎቻችን፥ መሬታችን ሁሉ፥ እርሻዎቻችን፥ መንጋዎቻችን፥ በጐቻችንና የመሰማሪያችን ቦታዎች ሁሉ፥ በፊትህ ናቸው፤ እንደ ወደድህ አድርጋቸው። 4እነሆ ከተሞቻችንና የሚኖሩባቸውም ሁሉ ባርያዎችህ ናቸው። መጥተህም ለዓይንህ መልካም የሆነውን አድርግ።” 5ሰዎቹ ወደ ሆሎፎርኒስ መጥተው ይህንኑ ነገሩት። 6እርሱም ከሠራዊቱ ጋር ወደ ባሕሩ ጠረፍ ወርደ፥ በተመሸጉት ከተሞችም የጦር ሰፈር አቆመ፤ እንዲረዱትም ከእነርሱ የተመረጡ ሰዎችን ወሰደ። 7እነሱና#3፥7 ሕዝቡ። በዙሪያውም ያሉ አገሮች ሁሉ አክሊል ደፍተው በጭፈራና በከበሮ ተቀበሉት። 8#ዘፀ. 34፥13፤ 2ዜ.መ. 17፥6።እርሱ ግን አገራቸውን ሁሉ አጠፋ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቆረጠ፤ ሕዝቦች ሁሉ ናቡከደነፆርን ብቻ እንዲያመልኩና ቋንቋዎችና ነገዶች ሁሉ አምላክ ብለው እንዲጠሩት፥ የምድሪቱን አማልክት እንዲያጠፋ ታዝዞ ነበርና። 9ከይሁዳ ተራሮች አንፃር በዶታን አጠገብ ወደሚገኝ ወደ ኤስድራሎን መጣ። 10በጌባና በሲቶፖሊስ መካከል ሰፈረ፥ ለሠራዊቱ ስንቅ ለመሰብሰብ በዚያ አንድ ወር ሙሉ ተቀመጠ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ