መጽሐፈ ዮዲት 2
2
በምዕራብ በኩል የተካሄደው ዘመቻ
1በዓሥራ ስምንተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር በሃያ ሁለተኛው ቀን በአሦሩ ንጉሥ በናቡከደነፆር ቤት ከዚህ በፊት እንደ ተናገረው አገሮቹን ሁሉ ለመበቀል ምክክር ተደረደ። 2ሹሞቹንና ታላላቅ ሰዎቹን ሁሉ ሰብስቦ ከእነርሱ ጋር ሚስጢራዊ እቅዱን በፊታቸው አስቀመጠ፥ የምድሪቱን ሁሉ ክፋት በአንደበቱ ተናገረ። 3ከአፉ የወጣውን ቃል አልታዘዝም ያለ ሥጋ#2፥3 ሰው። ሁሉ እንዲጠፋ ወሰኑ። 4እንዲህም ሆነ እቅዱን ከጨረሰ በኋላ የአሦር ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊት ዋና የጦር አዛዥ በደረጃ ከራሱ#2፥4 ከንጉሡ። ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነውን ሆሎፎርኒስን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ 5“የምድር ሁሉ ጌታ የሆነው ትልቁ ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከፊቴ ሂድና በኀይላቸው የታወቁትን ሰዎች ከአንተ ጋር መቶ ሃያ ሺህ እግረኛ ወታደሮችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞችን ውሰድ፤ 6ከአፌ የወጣውን ቃል አልታዘዙምና በምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ተገናኛቸው፤ 7መሬትና ውሃ እንዲያዘጋጁ ንገራቸው፥ በቁጣዬ በእነሱ ላይ እወጣለሁና፤ የምድርም ገጽ ሁሉ በሠራዊቴ#2፥7 ግሪኩ በኃይሌ ይላል። እግሮች ይሸፈናሉ፤ እንዲበረበሩም እተዋቸዋለሁ። 8ቁስለኞቻቸው ሸለቆዎችን እና ወራጅ ውሃዎችን ይሞላሉ፤ ወንዝም በሬሳዎቻቸው ተሞልቶ ይፈሳል። 9እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምርኮ አድርጌ እልካቸውዋለሁ። 10አንተ ግን ቀድመህ ሂድና ግዛቶቻቸውን ሁሉ ያዝልኝ፤ ራሳቸውን አሳልፈው ከሰጡህ ፍርዳቸውን እስከሚቀበሉበት ቀን ድረስ ጠብቀህ አቆያቸው። 11አንታዘዝህም ያሉትን ግን ዓይንህ አትተዋቸው#2፥11 አትራራላቸው።፤ በያዝከው ምድር ሁሉ ለሞትና ለብዝበዛ አሳልፈህ ስጣቸው። 12ሕያው ነኝና በመንግሥቴም ኃይል፥ የተናገርኩትን በእጄ እፈጽመዋለሁ። 13አንተም ጌታህ ከተናገረህ ነገሮች አንድስ እንኳ እንዳትተላለፍ፥ ነገር ግን እንዳዘዝሁህ ፈጽማቸው፤ ሳትዘገይም ፈጽመው።”
14ሆሎፎርኒስ ከጌታው ፊት ወጣ፥ የአሦርን ሠራዊት አዛዦችን፥ አለቆችና መኳንንት ሁሉ ጠራ። 15ጌታው እንዳዘዘው የተመረጡ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰልፈኞችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ቀስት ወርዋሪ ፈረሰኞችን ቆጠረ። 16ለጦርነትም አሰለፋቸው። 17ዕቃዎቻቸውን የሚሸከሙ እጅግ ብዙ ግመሎችን፥ አህዮችንና በቅሎዎች፤ እንዲሁም ለምግብ የሚሆኑ ስፍር ቍጥር የሌላቸው በጎችን፥ በሬዎችንና ፍየሎችን ወሰደ፤ 18ለእያንዳንዱ ሰው የሚሆን ስንቅ፥ ብዙ ወርቅና ብር ከንጉሡ ቤት ወሰደ። 19እርሱም ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ሆኖ ከንጉሡ ከናቡከደነፆር ቀድሞ ወደ ዘመቻ ለመሄድና በምዕራብ በኩል ያለ ምድርን ሁሉ በሠረገላዎች፥ በፈረሰኞችና በተመረጡ እግረኞች ሊሸፍኑ ወጡ። 20#መሳ. 7፥12፤ ኢዩ. 2፥2-11።ከእነሱም ጋር ብዛታቸው እንደ አንበጣና እንደ ምድር አሸዋ የሆኑ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ ሄዱ፤ ብዛታቸውም ቍጥር አልነበረውም።
የሆሎፎርኒስ ጥቃት ደረጃዎች
21ከነነዌ ከተማ ወጥተው ወደ ቤክቲሌት ሜዳ የሦስት ቀን ጉዞ ተጓዙ፤ ከቤክቲሌት አጠገብ በሚገኝ ከላይኛው ኬልቅያ በስተ ግራ በኩል ባለው ተራራ ሰፈሩ። 22ከዚያም ሆሎፎርኒስ#2፥22 ሆሎፎርኒስ የሚለው በግሪኩ የለም። ሠራዊቱን ሁሉ፥ እግረኞችን፥ ፈረሰኞችንና ሠረገላዎቹን ይዞ ወደ ተራራማው አገር ሄደ። 23ፉጥንና ሉድን ሰበራቸው፤ የሬስስን ልጆችን ሁሉና፥ በኬሌዎን በስተ ደቡብ አንጻር ባለ በረሃ የሚኖሩ የእስማኤልን ልጆች ማረካቸው። 24ኤፍራጥስን ተከትሎ፥ በመስጴጦምያ አልፎ በአብሮን ወንዝ ትይዩ ያሉ ምሽግ ያላቸውን ከተሞች ደምስሶ እስከ ባሕሩ ድረስ ሄደ። 25የኪልቅያን ግዛቶች ያዘ፤ የተቃወሙትንም ሁሉ መታ፤ በዓረብ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ ደቡብ ያፌት ግዛት መጣ። 26የምድያምን ልጆች ሁሉ ከበባቸው፥ መኖሪያዎቻቸውን አቃጠለ፥ መንጎቻቸውንም ዘረፈ። 27ስንዴ በሚታጨድበት ጊዜ ወደ ደማስቆ ሜዳ ወርዶ እርሻቸውን በሙሉ አቃጠለ፥ የበጐቻቸውንና የበሬዎቻቸውን መንጎች ለጥፋት ሰጣቸው፥ ከተሞቻቸውን በዘበዘ፥ ሜዳዎቻቸውን አጠፋ፥ ወጣቶቻቸውን ሁሉ በሰይፍ አፍ መታ። 28በባሕሩ ዳርቻ፥ በሲዶናና በጢሮስ በሚኖሩ ሁሉ፥ በሱርና በኦኪን በሚኖሩ ሁሉና በያምኒያ በሚኖሩ ሁሉ ፍርሃትና መንቀጥቀጥ ወደቀባቸው፤ በአዛጦንና በአስቀሎና የሚኖሩ እጅግ ፈሩት።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዮዲት 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ