መጽሐፈ መሳፍንት 6:3-6

መጽሐፈ መሳፍንት 6:3-6 መቅካእኤ

እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች መጥተው አገሩን ይወሩ ነበር። እነርሱም በምድሪቱ ላይ ሰፍረው እስከ ጋዛ ያለውን ሰብል በማጥፋት አንዳችም የእህልዘር አያስተርፉም፥ የበግም ሆነ የከብት ወይም የአህያ መንጋ አይተዉም ነበር። ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቁጠር አዳጋች ሲሆን፥ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር። ምድያማውያን እስራኤላውያንን ችግር ላይ ስለጣሏቸው፥ ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ጮኹ።