የያዕቆብ መልእክት 2:8-11

የያዕቆብ መልእክት 2:8-11 መቅካእኤ

በመጽሐፍ፥ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ የተጻፈውን ንጉሣዊ ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ። አድልዎ ብታደርጉ ግን ኃጢአት መሥራታችሁ ነው፤ እንደ ሕግ ተላላፊዎችም ትቈጠራላችሁ፤ ምክንያቱም ሕግን ሁሉ ብትፈጽሙ ነገር ግን በአንዱ ብትሰናከሉ፥ ሁሉን እንደ ተላለፋችሁ ይቈጠራል። “አታመንዝር” ያለ እርሱ ራሱ “አትግደል” ብሏል። ባታመነዝር፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል።