ወንድሞቼ ሆይ! ክቡር በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ በመሆናችሁ፥ አድልዎን አታድርጉ። የወርቅ ቀለበት ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤያችሁ ቢመጣ እንዲሁም ያደፈ ልብስ የለበሰ ድኻ ሰው ቢገባ፥ ያማረ ልብስ ለለበሰው የተለየ አክብሮት በማሳየት፥ “ለአንተ የሚሆን መልካም መቀመጫ ይኸውልህ” ብትሉትና ድኻውን ሰው ግን፥ “አንተ በዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ በታች በወለሉ ላይ ተቀመጥ” ብትሉት፥ በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን? ደግሞስ በክፉ ሐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን? የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱም ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን? እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን? እናንተ የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን? በመጽሐፍ፥ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ የተጻፈውን ንጉሣዊ ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ። አድልዎ ብታደርጉ ግን ኃጢአት መሥራታችሁ ነው፤ እንደ ሕግ ተላላፊዎችም ትቈጠራላችሁ፤ ምክንያቱም ሕግን ሁሉ ብትፈጽሙ ነገር ግን በአንዱ ብትሰናከሉ፥ ሁሉን እንደ ተላለፋችሁ ይቈጠራል። “አታመንዝር” ያለ እርሱ ራሱ “አትግደል” ብሏል። ባታመነዝር፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል። ስለዚህ ስትናገሩም ሆነ ስታደርጉ በነጻነት ሕግ እንደሚፈረድባቸው ሰዎች አድርጉ፤ ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታልና፤ ምሕረትም ፍርድን ያሸንፋል።
የያዕቆብ መልእክት 2 ያንብቡ
ያዳምጡ የያዕቆብ መልእክት 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የያዕቆብ መልእክት 2:1-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች