ኦሪት ዘፀአት 5:1-22

ኦሪት ዘፀአት 5:1-22 መቅካእኤ

ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’” ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ። እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት። የግብጽ ንጉሥም፦ “ሙሴና አሮን፥ ለምን ሕዝቡን ሥራቸውን ታስተዋላችሁ? ወደ ተግባራችሁ ሂዱ” አላቸው። ፈርዖንም፦ “እነሆ የምድሩ ሕዝብ አሁን በዝቶአል፥ እናንተም ሥራቸውን ታስፈቱአቸዋላችሁ” አለ። ፈርዖንም በዚያን ቀን የሕዝቡን አስገባሪዎች ሹማምንቶቹንም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “እንደ ቀድሞው ለጡብ ሥራ የሚሆን ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ፤ እነርሱ ራሳቸው ሄደው ገለባ ይሰብስቡ። ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ መሄድ እንፈልጋለን’ እያሉ ይጮኸሉ። ሥራውን እንዲሰሩት፥ የሃሰትን ቃላት እንዳያስቡ፥ በሰዎቹ ላይ ሥራው ይክበድባቸው።” የሕዝቡ አስገባሪዎችና ሹማምንቶቹም ወጡ፥ ሕዝቡንም አሉት፦ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ገለባ አልሰጣችሁም። እናንተ ሂዱ፥ ከምታገኙበትም ስፍራ ገለባ ሰብስቡ፤ ከሥራችሁ ግን ምንም አይጉደል።’” ሕዝቡም ለገለባ የሚሆን እብቅ ሊሰበስቡ በግብጽ ምድር ሁሉ ተበተኑ። አስገባሪዎቹም፦ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ” እያሉ አስቸኮሉአቸው። የፈርዖንም አስገባሪዎች፦ “የተወሰነላችሁን የጡብ ሥራ ትናንትናና ዛሬ ለምን እንደ ቀድሞው አልጨረሳችሁም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ። የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ ብለው ጮሁ፦ “ለምን አገልጋዮችህን እንዲህ ታደርጋለህ? ለአገልጋዮችህ ገለባ አልተሰጠም፥ ጡብ ሥሩ ይሉናል፤ እነሆ አገልጋዮችህ ተገረፍን፤ ይህም ሕዝብህን ሐጢአተኛ ያደርጋል።” እርሱም አላቸው፦ “ሰልችታችኋል፥ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለጌታም እንሠዋ’ ትላላችሁ። ስለዚህም ሂዱ፥ ሥሩ፤ ገለባ አይሰጣችሁም፥ የጡቡን ቍጥር ግን ታመጣላችሁ።” የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጉድሉ” በተባሉ ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን ቆመው አገኙአቸው። እነርሱም፦ “ጌታ እናንተ ላይ ይፍረድባችሁ፥ ሽታችንን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አግምታችሁታልና፥ እንዲገድሉንም ሰይፍን በእጃቸው አስቀምጣችኋዋልና” አሉአቸው። ሙሴም ወደ ጌታ ተመለሰና፦ “ጌታ ሆይ፥ ለምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ለምንስ ላክኸኝ?

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}