መጽሐፈ ባሮክ 1
1
ባሮክና አይሁዳውያን በባቢሎን
1 #
ኤር. 36፥4። የሂልቅያ ልጅ፥ የሃሳዲያ ልጅ፥ ሴዴቅያ ልጅ፥ ማህሴያ ልጅ፥ የኔሪያ ልጅ ባሮክ በባቢሎን የጻፈው የመጽሐፉ ቃል ይህ ነው፤ 2በአምስተኛው ዓመት ከወሩ በሰባተኛው ቀን ከለዳውያን ኢየሩሳሌምን በያዙአትና በእሳት በአቃጠሉአት ጊዜ፤
3 #
2ነገ. 24፥8-17። ባሮክ የዚህን መጽሐፍ ቃል ለይሁዳ ንጉሥ ለኢኮንያን ልጅ ለኢዮአቄምና መጽሐፉን ለመስማት ለመጣው ሕዝብ አነበበው፤ 4ባለ ሥልጣኖች፥ ለመሳፍንት፥ ለሽማግሌዎች፥ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በባቢሎን በሱድ ወንዝ አጠገብ ለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ አነበበ። 5በዚህን ጊዜ አለቀሱ፥ ጾሙ፥ በጌታም ፊት ጸለዩ። 6እያንዳንዱ መስጠት እንደሚችለው መጠን ገንዘብ ሰበሰቡ፤ 7እርሱንም ወደ ሻሉም ልጅ፥ ወደ ሂልቅያ ልጅ፥ ወደ ሊቃ ካህኑ ኢዮአቄም፥ ወደ ካህናቱ፥ በኢየሩሳሌም ከእርሱ ወደነበሩት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ላኩት። 8በዚያው ጊዜ፥ በሲቫን ወር በዐሥረኛው ቀን፥ ከቤተ መቅደስ ተወስደው የነበሩትን የጌታን ቤት ዕቃዎች ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ ወሰዳቸው፤ እነዚህ የብር ዕቃዎች የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያ የሠራቸው ነበሩ፤ 9ኢዮአቴም የሠራቸውም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢየንያንን ማርኮ እንዲሁም ሹማምንቱን፥ ምርኮኞቹን፥ ባለሥልጣኖቹንና የአገሩን ሕዝብ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ከወሰደ በኋላ ነው።
ወደ ኢየሩሳሌም የተላከ ደብዳቤ
10እንዲህም አሉ፦ “እነሆ ገንዘብ ልከንላችኋል፤ ስለዚህ በገንዘቡ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኃጢአት መሥዋዕት፥ ዕጣን ግዙ፥ የእህል መሥዋዕት አዘጋጁ፤ በጌታ በአምላካችን መሠዊያ ላይ አቅርቡት፤ 11የምድር ቀኖቻቸው እንደ ሰማይ ቀኖች ረጅም እንዲሆኑላቸው፥ ስለ ባቢሎን ንጉሥ ስለ ናቡከደነፆር ሕይወትና ስለ ልጁ ሰለ ብልጣሶር ሕይወት ጸልዩ። 12ጌታ ኃይል ይሰጠናል፥ ብርሃንም ዐይኖቻችን። በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር ጥላ ሥርና በልጁ በብልጣሶር ጥላ ሥር እንኖራለን፥ ብዙ ቀኖችም እናገለግላቸዋለን፥ በፊታቸውም ሞገስን እናገኛለን። 13እኛ በጌታ በአምላካችን ላይ ኃጢአትን ሰርተናልና፥ እስከዚችም ቀን ድረስ የጌታ መዓቱና ቁጣው ከኛ አልራቀምና ወደ ጌታ ወደ አምላካችን ጸልዩልን። 14በበዓል ቀኖችና በተመደቡ ቀኖችና ንስሐችሁን በጌታ ቤት ለማድረግ ይህንን የምንልክላችሁን መጽሐፍ አንብቡ።”
የኃጢአት ንስሐ
15እንዲህም በሉ፤ ጽድቅ የጌታ የአምላካችን ነው፥ ነገር ግን ዛሬ በእኛ ላይ የፊት ኅፍረት ነው፥ እንዲሁም በይሁዳ ሰዎች፥ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፥ 16ለንጉሦቻችን፥ ለገዢዎቻችን፥ ለካህኖቻችን፥ ለነብዮቻችን፥ ለአባቶቻችን የፊት ኅፍረት ነው፥ 17ምክንያቱም በጌታ ፊት በድለናልና፤ 18አልታዘዝነውም፥ የጌታ የአምላካችንን ድምጽ አልሰማንም፥ በፊታችን ባስቀመጣቸው በጌታ ትእዛዞች መሠረት አልሄድንምና፤ 19ጌታ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ከአወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለጌታ አምላካችንን አልታዘዝነውም፥ ድምጹንም ባለመስማት ቸልተኞች ሆነናል። 20#ዘዳ. 28፥15-68።ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ሊሰጠን አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር በአወጣበት ቀን ጌታ ለባርያው በሙሴ ያዘዘው ክፉ ነገርና መርገም እስከ ዛሬ ጸንቶብናል። 21ወደ እኛ በላካቸው በነቢያት ቃል በኩል የጌታ አምላካችንን ቃል አልሰማንም። 22ነገር ግን ሌሎች አማልክትን በማገልገል፥ በጌታ አምላካችን ፊት ክፉውን ሁሉ በማድረግ፥ እያንዳንዳችን የገዛ ልባችንን ክፉ ሐሳብ ተከተልን።
Currently Selected:
መጽሐፈ ባሮክ 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ