2ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:4-6

2ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:4-6 መቅካእኤ

ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአባት እንደተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት የሚመላለሱ ሆነው በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ። ፍቅር ይህ ነው፥ እርሱም በትእዛዛቱ መመላለስ ነው፤ ትእዛዙ ይህ ነው፥ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደ ሰማችሁት፥ በእርሱ ተመላለሱ።