2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:8-11

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:8-11 መቅካእኤ

አዎ፥ ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በጌታ ዘንድ መኖር እንመርጣለን። ስለዚህ በማደሪያችን ሆንን ወይም ተለይተን ሄድን፥ እርሱን ደስ የምናሰኝ መሆንን ነው የምንፈልገው። መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን። እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።