2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-12

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-12 መቅካእኤ

ከየአቅጣጫው መከራን እንቀበላለን እንጂ አንጨነቅም፤ ግራ እንጋባለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤ እንሰደዳለን እንጂ አንተውም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን እንዲገለጥ፥ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን እንዲገለጥ፥ እኛ ሕያዋን የሆንን ስለ ኢየሱስ ስንል ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለን። ስለዚህ ሞት በእኛ፥ ሕይወት ግን በእናንተ ይሠራል።