1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:17-19

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:17-19 መቅካእኤ

የእግዚእብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል። ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። በዚያው መንፈስ በእስር ቤት ወዳሉት ነፍሳት ሄዶ ሰበከላቸው፤