1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:1-3

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:1-3 መቅካእኤ

እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዓይነት አንዳንዶች በቃሉ የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል። የሚሳቡትም አክብሮት የተሞላውንና ንጹሕ ኑሮአችሁን ሲመለከቱ ነው። ለእናንተም ቢሆን ውበታችሁ ውጫዊ የሆነ፥ ሹሩባ በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና የከበረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤