1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 4
4
የኤማሁስ ጦርነት
1ጐርጊያስ አምስት ሺህ እግረኞችና አንድ ሺህ ምርጥ ፈረሰኞች ይዞ በሌሊት ሄደ፤ 2ይህን ማድረጉም በአይሁዳውያን ሠፈር በድንገት ደርሶ በእነርሱ ላይ ድንገተኛ አደጋ ለመጣል ነው። የኢየሩሳሌም ምሽግ ሰዎች የሱ መሪዎች ሆነው ያገለግሉት ነበር። 3ይሁዳ ወሬውን አስቀድሞ በመስማቱ በኤማሁስ የነበረውን የንጉሡን ጦር ሠራዊት ለመውጋት ከጀግኖቹ ጋር ሆኖ ሄደ፤ 4በዚያን ጊዜ የጐርጊያስ ሰዎች ከሠፈር ውጪ ተበታትነው ይገኙ ነበር። 5ጐርጊያስ ወደ ይሁዳ ሠፈር ሌሊት ደረሰ፤ እዚያ ማንንም ሳያገኝ ቀርቶ፥ “ሸሽተውን ሄደዋል” ብሎ አይሁዳውያንን በተራራዎቹ ላይ ይፈልግ ጀመር። 6በነጋ ጊዜ ይሁዳ ከአምስት ሺህ ሰዎች ጋር በማዳው ላይ ታየ፤ ግን ሰዎቹ ያስፈልጓቸው የነበሩትን የጦር መሣሪያዎችና ሰይፎች አልያዙም ነበር። 7ያንጊዜ ካሉበት ስፍራ ሆነው የተጠናከረውንና የመሸገውን የአረማውያንን ሠፈር ተመለከቱ፤ በሠፈሩ ዙሪያ ፈረሰኞች ነበሩ፤ ሁሉም ዓዋቂዎችና የጦር ልምምድ ያላቸው ነበሩ። 8ይሁዳ ሰዎቹ እንዲህ አላቸው፥ “ብዛታቸውን በማየት አትፈሩ፤ በውጊያቸውም አትደንግጡ፤ 9ፈርዖን የጦር ሠራዊቱን ይዞ አባቶቻችንን ሲያሳድድ እነርሱ በቀይ ባሕር ላይ እንዴት እንደዳኑ አስታውሱ፤ 10አሁንም ወደ ሰማይ እንጩህ፤ የሚያስብልን ከሆነ ለአባቶቻችን የገባላቸውን ቃል ኪዳን ያስታውሳል፤ ያንን ሠራዊትም ዛሬ በፊታችን ይደመስሰዋል፤ 11አረማውያን ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን የሚታደግና የሚያድን መኖሩን ያውቃሉ።” 12እነዚያ የባዕድ አገር ሰዎች ቀና ብለው የአይሁዳውያንን ወደ እነርሱ መምጣት አዩ፤ 13ጦርነት ለመግጠም ከሠፈራቸው ወጡ፤ የይሁዳ ሰዎች መለከት ነፉ፤ 14ጦርነትም ገጠሙ። አረማውያን ሕዝቦች ተሸነፉ፤ ወደ ሜዳውም ሸሹ። 15ነገር ግን በስተ ኋላ የነበሩት ሁሉ በሰይፍ ተመትተው ወደቁ። እስከ ጌዜሮንና እስከ ኤዶምያስ ሜዳ ድረስ፥ እስከ አዛጦንና እስከ ያምንያ ድረስ ተከታተሏቸው፤ ጠላት ሦስት ሺህ የሚያህሉ ሰዎች በዚያ አጣ። 16ይሁዳ ከወታደሮቹ ጋር ጠላቶቹን ከማሳደድ ተግባሩ ተመልሶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፥ 17“ሌላ ጦርነት ስለሚጠብቀን አሁን ለምርኮ አትቸኩሉ፤ 18ጐርጊያስና ወታደሮቹ በተራራው ላይ በአጠገባችን ናቸው፤ ጠላቶቻችንን ተቋቋሟቸው፤ ውጓቸው፤ ከዚህ በኋላ ምርኳችሁን ያለ ስጋት መሰብሰብ ትችላላችሁ”። 19ይህን ብሎ እንዳበቃም የጠላት ወታደሮች በተራራው ጫፍ ላይ ሆነው በመሰለል ላይ ሳሉ ታዩ። 20የእነርሱ ወታደሮች መሸነፋቸውንና ሰፈራቸውም በመቃጠል ላይ መሆኑን ተመለከቱ፤ የሚታየውም ጭስ የሆነውን ነገር በግልጽ ያስረዳ ነበር። 21ይህን ባዩ ጊዜ በፍርሃት ተዋጡ፤ እንዲሁም ለውጊያ የተዘጋጁትን የይሁዳን ጦር ሠራዊት በሜዳው ላይ አዩና 22ሁሉም ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ሸሹ። 23ከዚህ በኋላ ይሁዳ ሠፈራቸውን ለመዝረፍ ተመልሶ መጣ፤ ብዙ ወርና ብር፥ ሐሞራዊ ከፋይና ቀይ ጨርቆች እንዲሁም ብዙ ሀብቶችን ወሰደ። 24በመልሱም ጉዞ ላይ፥ “እግዚአብሔር ደግና ፍቅሩም ዘላለማዊ ነው እያሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ ተመለሱ”። 25ያ ቀን በእስራኤል ትልቅ የነጻነት ቀን ሆነ። 26እነዚያ ሸሽተው ያመለጡ የባዕድ አገር ሰዎች ወደ ሊስያስ መጥተው የሆነውን ነገር ሁሉ አወሩለት።፥ 27ይህ ወሬ በጣም አስደነገጠው፤ ፍርሃትም አሳደረበት፤ ምክንያቱም የእስራኤል ጉዳይ እርሱ እንዳሰበው አልተፈጸመለትም፤ ውጤቱም የንጉሡን ትእዛዝ የሚቃወም ሆኖ ተገኘ።
የመጀመሪያው የሊስያስ ዘመቻ
28ቀጥሎም ባለው ዓመት አይሁዳውያንን ለመውጋት ሥልሳ ሺህ ምርጥ እግረኞችንና አምስት ሺህ ፈረሰኞችን ሰበሰበ። 29ወደ ኤዶምያስ ሄደው በቤተሱር ሰፈሩ፤ ይሁዳ ሊገጥማቸው ዐሥር ሺህ ሰው ይዞ ሄደ። 30ይህን ከባድ ሠራዊት ባየ ጊዜም እንዲህ ብሎ ጸለየ “የእስራኤል አዳኝ ሆይ አንተ የተመሰገነህ ነህ፤ በአገልጋይህ በዳዊት እጅ የኃይለኛውን ተዋጊ ሰው ኃይል ያንኮታኮትህ ነህ፤ 31እንዲሁም አሁን ይህን ሠራዊት በሕዝብህ በእስራኤል እጅ አጥፋው፤ በእግረኛ ጦራቸውና በፈረሰኛ ጦራቸው ይፈሩ፤ 32ፍርሃትን አሳድርባቸው፤ እፍረተ ቢሱን ጦራቸውን አቅልጠው፤ ድል ተነሥተው ይንቀጥቀጡ፤ 33በሚወዱህ ሰዎች ሰይፍ ላይ ጣላቸው፤ ስምህን የማያውቁ ሰዎች ሁሉ በመዝሙር ያመስግኑህ”። 34ውግያው ተጀመረና በጨበጣ ውግያ ከሊስያስ ጦር ሠራዊት አምስት ሺህ ሰዎች ያህል ሞቱበት። 35የሠራዊቱን ሽንፈትና የይሁዳ ሠራዊትን ድፍረት ባየ ጊዜ፥ እንዲሁም የይሁዳ ወታደሮች ለመኖር ወይም በጀግንነት ለመሞት ምን ያህል ዝግጁዎች መሆናቸውን ባየ ጊዜ ሊስያስ የባዕድ አገር ወታደሮችን ለመሰብሰብና ተጠናክሮ ወደ ይሁዳ አገር ተመልሶ ለመመጣት ወደ አንጾኪያ ሄደ።
የቤተ መቅደስ መንጻትና ዳግም መቀደስ
36ይሁዳና ወንድሞቹ፥ “እነሆ ጠላቶቻችን ተሸንፈዋል፤ እንሂድና ቤተ መቅደሱን እናንጻ፥ እናክብረው” አሉ። 37ሠራዊቱ ሁሉ ተሰበሰቡና ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ወጡ። 38ቤተ መቅደሱ ባዶ ሆኖ፥ መሠዊያው ረክሶ፥ መዝጊያዎቹ ተቃጥለው አዩ፤ በግቢው ውስጥ የበቀለው ሣርና ቅጠሉ በጫካ ውስጥ ወይም በተራራ ላይ እንደሚታየው ዓይነት ነበር፤ መጋዘኖቹም ፈራርሰዋል። 39በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ታላቅ ኀዘን አደረጉ፥ ራሳቸው ላይ አመድ ነሰነሱ። 40በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ፥ መለከቱ በተነፋ ጊዜ ወደ ሰማይ ጮኹ። 41ቤተ መቅደሱ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ በከተማዋ ምሽግ ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንዲዋጉ ይሁዳ ከእርሱ ሰዎች እንዳንዶቹን ጠርቶ አዘዛቸው፥ 42ከዚህ በኋላ ያልረከሱትንና የሙሴን ሕግ የሚያፈቅሩትን ካህናት መረጠ፤ 43እነርሱ ቤተ መቅደሱን አነጹ፤ የረከሱትን ደንጊያዎችን በቆሻሻ ቦታ ጣሏቸው። 44የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ይሠውበት የነበረውን የረከሰውን መሠዊያ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠያየቁ፤ 45አረማውያን አርክሰውት ስለ ነበረ ውርደት እንዳይሆንባቸው ፈርተው ለማፍረስ አሰቡ፤ ስለዚህ አፈረሱት፤ 46ስለ ድንጋዮቹ ነቢይ መጥቶ ምን ማድረግ እንደሚገባ እስኪናገር በደኀና ቦታ ከቤተ መቅደሱ በላይ በሚገኘው ከረብታ ላይ አስቀመጧቸው፤ 47በሙሴ ሕግ መሠረት ያልተጠረቡ ድንጋዮች አምጥተው እንደ በፊቱ ዓይነት አድርገው አዲስ መሠዊያ ሠሩ። 48የቤተ መቅደሱን ውጭውንና ውስጡን አደሱት፤ ግቢውን ቀደሱት፤ 49አዳዲስ የተቀደሱ ዕቃዎችን ሠርተው በቤተ መቅደሱ ውስጥ መቅረዙን፥ የዕጣን ማጨሻውን፥ ጠረጴዛውን አስገቡ። 50በመሠዊያው ላይ ዕጣን አጨሱ፤ በመቅደሱ ውስጥ ብርሃን የሚሰጡትን የመቅረዙን መብራቶች ዘረጉና አበሩ። 51በጠረጴዛው ላይ ኀብስት አስቀመጡ፤ መጋረጃዎቹን ዘረጉ፤ ሥራዎቹንም ሁሉ ፈጸሙ። 52ቂስለው በሚባለው በዘጠነኛው ወር በሃያ አምስት (ታኀሣሥ 14 በመቶ አርባ ስምንት ዓመት) ጎህ ሲቀድ ተነሡ፤ 53የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች በሚቀርቡበት ቦታ እነርሱ በሠሩት በዲሱ መሠዉያ ላይ በሙሴ ሕግ መሠረት መሥዋዕት አቀረቡ። 54በዚያው አረማውያን ባረከሱበት ዓመትና ዕለት መሠዊያው በመዝሙር፥ በበገና፥ በክራር፥ በጸናጽል ተመረቀ።፥ 55ሕዝቡ ሁሉ ለመስገድ በግንባሩ ተደፋ፤ ወደ ድል ለመራቸው አምላክም ምስጋና አቀረቡ። 56የመሠዊያውን ምረቃ በዓል ስምንት ቀን አከበሩ፤ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን፥ የአንድነትና የምስጋና መሥዋዕቶችንም በታላቅ ደስታ አቀረቡ። 57የቤተ መቅደሱን ፊት በር በወርቅ አክሊሎችና ጋሻዎች አጌጡት መግቢያዎቹንና ቤቶቹን አደሷቸው፤ መዝጊያዎችም አደረጉላቸው። 58በሕዝቡ መካከል ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከአረማውያን የመጣባቸው ውርደት ተደመሰሰ። 59ይሁዳና ወንድሞቹ፤ የእስራኤልም ሕዝቡ በሙሉ በሃያ አምስት በቂስለው ወር ጀምሮ ስምንት ቀን ሙሉ በየዓመቱ በእነርሱ ጊዜ የመሠዊያው ምረቃ ቀኖች በታላቅ ደስታ እንዲከበሩ ወሰኑ። 60እንደ ቀድሞው አረማውያን መጥተው እነዚህን ቦታዎች እንዳይበዘብዙ በዚያን ጊዜ ከፍተኛ መካበቢያዎችና የግንብ ምሽጐች በጽዮን ተራራ ዙሪያ ሠሩ። 61ይሁዳም ጠባቂ ወታደሮችን አሠማራ። በኤዶምያስ በኩል ሕዝቡም ምሽግ እንዲኖረው ቤተሱርን አጠናከረ።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ