ከመጀመሪያው የነበረውን፥ የሰማነውን፥ በዐይኖቻችንም ያየነውን፥ የተመለከትነውንና እጆቻችንም የዳሰሱትን፥ ስለ ሕይወት ቃል እንናገራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ፥ አይተነዋል እንመሰክራለንም፥ በአብ ዘንድ የነበረውን ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን። ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። ደስታችን ሙሉ እንዲሆን ይህን እንጽፍላችኋለን። ከእርሱ የሰማነውና ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም። ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን እያልን በጨለማ ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ዘንድ የለም። ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን የታመነና ጻድቅ ነው፥ ከዓመፃም ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1 ያንብቡ
ያዳምጡ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች