1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:3-5

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:3-5 መቅካእኤ

ያለኝን ሁሉ ለድኾች ባካፍል፥ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት አሳልፌ ብሰጥ፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሳል፤ ቸርነትንም ያደርጋል። ፍቅር አይቀናም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም።