1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8
8
የብንያም ትውልድ
1ብንያምም በኩሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፥ 2አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ። 3ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም አዳር፥ ጌራ፥ አቢሁድ፥ 4አቢሱ፥ ናዕማን፥ ኦሖዋ፥ 5ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም ናቸው። 6እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ 7ናዕማን፥ አኪያ፥ ሔግላ የተባለው ጌራ ዖዛንና አሒሑድን ወለደ። 8ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን እንዲሄዱ ካሰናበተ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ። 9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥ 10ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ። 11ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ። 12የኤልፍዓልም ልጆች፤ ዔቤር፥ ሚሻም አኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ ነበሩ፤ 13በሪዓና ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ 14አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥ 15ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥ 16ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ የበሪዓ ልጆች ነበሩ። 17ዝባድያ፥ ሜሱላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፥ 18ይሽምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ የኤልፍዓል ልጆች ነበሩ። 19ያቂም ዝክሪ፥ ዘብዲ፥ 20ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ 21ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ፤ 22ይሽጳን፥ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ 23ዓብዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፥ 24ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥ 25ዩፍደያና ፋኑኤል ተብለው የሚጠሩ ናቸው። 26ሸምሽራይ፥ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ 27ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች ነበሩ። 28እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
29የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው በገባዖን የተቀመጠው የገባዖን አባት ይዒኤል፥ 30የበኩር ልጁ ዓብዶን፥ ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥ 31ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር፥ 32ሳምአን የወለደው ሚቅሎት ነበሩ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ። 33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ። 34የዮናታንም ልጅ መሪ-በኣል ነበረ፤ መሪ-በኣልም ሚካን ወለደ። 35የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ። 36አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ። 37ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁም ረፋያ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል ነበሩ፤ 38ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሽዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን ይባሉ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ። 39የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኩሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት ነበሩ። 40የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኃያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ ኀምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ