ትንቢተ ዘካርያስ 8:3-8

ትንቢተ ዘካርያስ 8:3-8 አማ05

እኔ እንድኖርባት ወደ ተቀደሰችው ከተማዬ ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ የታመነች ከተማ በመሆን ትታወቃለች፤ እኔ የሠራዊት አምላክ የምኖርበት ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ተብሎ ይጠራል፤ ሰዎች ረጅም ዕድሜ ስለሚኖሩ ሽማግሌዎችና አሮጊቶች ምርኲዝ እየያዙ በመሄድ በኢየሩሳሌም አደባባዮች እንደገና ይቀመጣሉ፤ መንገዶችዋም ሁሉ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንደገና የተሞሉ ይሆናሉ። “በእነዚህ ቀኖች ከሕዝቡ ለተረፉት ይህ የማይቻል ነገር ቢመስልም እንኳ በውኑ ለእኔ የማይቻል ነገር አለን? እኔ ሕዝቤን በስደት ከሚኖሩበት ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋቸዋለሁ፤ መልሼ በማምጣት በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ።