ትንቢተ ዘካርያስ 4:8-10

ትንቢተ ዘካርያስ 4:8-10 አማ05

እንደገናም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጥለዋል፤ እጆቹም ይፈጽሙታል፤ ያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”