መጽሐፈ መዝሙር 44:1-3

መጽሐፈ መዝሙር 44:1-3 አማ05

አምላክ ሆይ! በጥንት ዘመን ያደረግኸውን ሁሉ በጆሮአችን ሰማን፤ የቀድሞ አባቶቻችንም በዘመናቸው ስላደረግሃቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ነግረውናል። በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል። እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።