መጽሐፈ መዝሙር 27:9-10

መጽሐፈ መዝሙር 27:9-10 አማ05

አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም። አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ እግዚአብሔር ዘወትር ይቀበለኛል።