መጽሐፈ መዝሙር 18:4-6

መጽሐፈ መዝሙር 18:4-6 አማ05

የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ። የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ። መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት፤ በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴንም አደመጠ።