መጽሐፈ መዝሙር 145:13-16

መጽሐፈ መዝሙር 145:13-16 አማ05

ግዛትህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። መንግሥትህም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ የታመነ ነው፤ እርሱ የሚያደርገው ሁሉ መልካም ነው። የሚንገዳገዱትን ይደግፋል፤ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። ሁሉም በተስፋ ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ አንተም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ። እጅህን ከፍተህ የእያንዳንዱን ሕያው ፍጥረት ፍላጎት ታረካለህ።