የማቴዎስ ወንጌል 15:13-21

የማቴዎስ ወንጌል 15:13-21 አማ05

እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል፤ እነርሱ ዕውሮችና ዕውሮችን የሚመሩ ስለ ሆኑ ተዉአቸው፤ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም በጒድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።” ጴጥሮስ ግን ኢየሱስን “የምሳሌውን ትርጒም አስረዳን” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተም እስከ አሁን ገና የማታስተውሉ ናችሁን? ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ ወርዶ ወደ ውጪ እንደሚወጣ አታስተውሉምን? ከአፍ የሚወጣው ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውን የሚያረክሰውም እርሱ ነው። ክፉ ማሰብ፥ ሰው መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት ማድረግ፥ መስረቅ፥ በሐሰት መመስከር የሰውን ስም ማጥፋት፥ ይህ ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣል። ሰውን የሚያረክሱ እነዚህ ናቸው እንጂ ባልታጠበ እጅ መብላትስ አያረክሰውም።” ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና ከተሞች ሄደ፤

ተዛማጅ ቪዲዮዎች