ኦሪት ዘሌዋውያን 9
9
አሮን ለእግዚአብሔር ያቀረበው መሥዋዕት
1ሰባት ቀን የቈየው የክህነት አሰጣጥ ሹመት በተፈጸመ ማግስት ሙሴ አሮንንና ልጆቹን፥ እንዲሁም የእስራኤልን መሪዎች ጠራ፤ 2አሮንንም እንዲህ አለው፤ “ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ የበግ አውራ ወስደህ ወይፈኑን ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ የበግ አውራውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርብ። 3ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል፥ ምንም ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ጥጃና የአንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያመጡ ንገራቸው። 4እንዲሁም አንድ ወይፈንና አንድ የበግ ጠቦት ለአንድነት መሥዋዕት ያምጡ፤ እነዚህንም በዘይት ከታሸ የእህል መባ ጋር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ስለሚገለጥላቸው ይህን ሁሉ ያድርጉ።”
5እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ ድንኳኑ ፊት ለፊት አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለመስገድ ወደዚያ ተጠግተው ቆሙ። 6ሙሴም “የእግዚአብሔር ክብር ስለሚገለጥላችሁ ይህን ሁሉ እንድታደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።” አላቸው። 7ከዚህም በኋላ ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፤ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የራስህን ኃጢአትና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ፤ ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አቅርብ።” #ዕብ. 7፥27።
8አሮንም ወደ መሠዊያው ሄዶ መጀመሪያ ስለ ራሱ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ ዐረደ፤ 9ልጆቹም ደሙን ወደ እርሱ አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በጣቱ እያጠቀሰ በመሠዊያው ላይ ያሉትን ጒጦች ቀባ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰ፤ 10ከዚህም በኋላ ስቡን፥ ኲላሊቶቹን እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነውን ወስዶ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤ 11ሥጋውንና ቆዳውን ግን ከሰፈር ውጪ አውጥቶ አቃጠለው።
12የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውንም እንስሳ ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን ወደ እርሱ አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨ፤ 13ጭንቅላቱንና ሌላውንም ሥጋ በየብልቱ ከፋፍለው አመጡለት፤ አሮንም ያን ሁሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው። 14ከዚህ በኋላ ሆድ ዕቃውንና የኋላ እግሮቹን በውሃ አጥቦ በመሠዊያው ላይ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ላይ በማኖር አቃጠለው።
15ከዚያም በኋላ ካህኑ የሕዝቡን መባ አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን ተባዕት ፍየል ወስዶ ዐረደው፤ እርሱንም ስለ ራሱ ኃጢአት ባቀረበው ዐይነት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። 16ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርበውንም እንስሳ አምጥቶ በሥርዓቱ መመሪያ ሕግ መሠረት ሠዋው። 17የእህሉንም መባ አቀረበ፤ ከዱቄቱም በእፍኙ ሙሉ ወስዶ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤ ይህም ለሚቃጠል መሥዋዕት ጧት ከሚቀርበው ጋር ተጨማሪ መሆኑ ነው። 18በሬውንና የበግ አውራውን ዐርዶ ስለ ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት በማድረግ አቀረበ፤ ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ተቀብሎ ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨው፤ #ዘሌ. 3፥1-11። 19አሮንም የወይፈኑንና የበግ አውራውን ስብ ሁሉ ማለትም ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን የሚሸፍነውን ስብ ምርጥ የሆነውን ክፍል፥ ኲላሊቶቹንና በእነርሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ፥ 20በእንስሶቹ ፍርምባ ጫፍ ላይ በመደረብ ያን ሁሉ ወስደው በመሠዊያው ላይ አኖሩት፤ አሮንም ስቡን በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤ 21ፍርምባዎቹንና በስተቀኝ በኩል ያሉትን የኋላ እግሮች ሙሴ ባዘዘው መሠረት በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ አቀረበው።
22አሮንም ይህን ሁሉ መሥዋዕት አቅርቦ እንደ ጨረሰ እጆቹን በሕዝቡ ላይ ዘርግቶ ከባረካቸው በኋላ ወረደ፤ #ዘኍ. 6፥22-26። 23ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ሕዝቡን ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤ 24እሳትም በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ፥ በመሠዊያው ላይ የነበረውን መሥዋዕትና ስብ ሁሉ በላ፤ ሕዝቡ ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በምድር ላይም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 9: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997