ሰቈቃወ ኤርምያስ መግቢያ
መግቢያ
ሰቈቃወ ኤርምያስ፥ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ዓመት ኢየሩሳሌም በመፍረስዋና ሕዝብዋም በመሰደዳቸው ምክንያት የቀረቡ አምስት የሐዘን ቅኔዎች ቅንብር ነው። የመጽሐፉ አብዛኛው ክፍል ስለ ለቅሶና ስለ ሐዘን የሚያወራ ቢሆንም እንኳ፥ በእግዚአብሔር ስለ መታመንና በተስፋ ስለ መኖር የሚናገር ክፍልም ይገኝበታል፤ እነዚህን ቅኔዎች አይሁድ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ዓመት በሀገሪቱ ላይ የደረሰውን ጥፋት ለማስታወስ በየዓመቱ በጾምና በሐዘን የአምልኮ ሥርዓቶችን በሚፈጽሙባቸው ቀኖች ውስጥ ይጠቀሙባቸዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የመጀመሪያው ሰቆቃ (1)
የኢየሩሳሌም መከራና ሐዘን (1፥1-22)
ሁለተኛው ሰቆቃ (2)
እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ላይ ያመጣው ቅጣት (2፥1-22)
ሦስተኛው ሰቆቃ (3)
ገና ተስፋ ያለ መሆኑ (3፥1-66)
አራተኛ ሰቆቃ (4)
የኢየሩሳሌም ጥፋት (4፥1-22)
አምስተኛው ሰቆቃ (5)
ምሕረት ለማግኘት ጸሎት (5፥1-22)
Currently Selected:
ሰቈቃወ ኤርምያስ መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997