መጽሐፈ ኢያሱ 6:1-3
መጽሐፈ ኢያሱ 6:1-3 አማ05
እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ የኢያሪኮ ቅጽር በሮች ተዘግተው ነበር፤ ወደ ከተማይቱ መግባትም ሆነ መውጣት የሚችል ማንም አልነበረም፤ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ኢያሪኮን ከንጉሥዋና ከወታደሮችዋ ጋር በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተና ወታደሮችህ እስከ ስድስት ቀን ድረስ በቀን አንድ ጊዜ የከተማይቱን ቅጽር በሰልፍ ትዞሩአታላችሁ።

