የዮሐንስ ወንጌል 4:34-35

የዮሐንስ ወንጌል 4:34-35 አማ05

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው። እናንተ ‘ገና አራት ወር ቀርቶታል፤ ከዚያም በኋላ መከር ይሆናል’ ትሉ የለምን? እኔ ግን ‘ቀና በሉና እርሻዎቹ ለመከር እንደ ደረሱ ተመልከቱ’ እላችኋለሁ።