የዮሐንስ ወንጌል 1:41-42

የዮሐንስ ወንጌል 1:41-42 አማ05

እንድርያስ በመጀመሪያ ወደ ወንድሙ ወደ ስምዖን ሄደና “መሲሕን አገኘነው!” አለው። (መሲሕ ማለት ክርስቶስ ማለት ነው።) ከዚህ በኋላ እንድርያስ ስምዖንን ወደ ኢየሱስ አመጣው። ኢየሱስም ትኲር ብሎ ተመለከተውና “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ኬፋ ትባላለህ” አለው። (ኬፋ ማለት ጴጥሮስ ወይም አለት ማለት ነው።)