ትንቢተ ኤርምያስ 45

45
እግዚአብሔር ለባሮክ የሰጠው ተስፋ
1የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ባሮክ በቃል የነገርኩትን ሁሉ በብራና ጥቅል ጻፈው፤ #2ነገ. 24፥1፤ 2ዜ.መ. 36፥5-7፤ ዳን. 1፥1-2። 2የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ስለ ባሮክ የተናገረውን እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ 3እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኝ ምንም ዕረፍት ሳይኖረኝ በመቃተት ደክሜአለሁና ወዮልኝ!
4“ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ይህንንም በምድር ሁሉ ላይ አደርጋለሁ፤ 5ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ