በዚህ ዓለም ለሚፈጸም ለማናቸውም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የወሰነለት ዘመንና ጊዜ አለው፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፥ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀል ጊዜ አለው። ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለመገንባት ጊዜ አለው፤ ለማፍረስም ጊዜ አለው። ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለመጨፈርም ጊዜ አለው። ድንጋይ ለመበተን ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለማቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው። ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ የጠፋውን ላለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፤ ለመጣልም ጊዜ አለው። ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለንግግርም ጊዜ አለው። ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው። ታዲያ፥ ሠራተኛ ከድካሙ የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? የሰው ልጆች እንዲደክሙበት እግዚአብሔር የሰጣቸውን የከባድ ሥራ ጭነት ተመለከትኩ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገር ጊዜ በመወሰን ሁሉን ነገር ውብ አድርጎ ሠርቶታል፤ ዘለዓለማዊነትንም በሰው ልቡና አሳድሮአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ያውቅ ዘንድ ለሰው የተሰጠው ዕውቀት ሙሉ አይደለም። ስለዚህ ሰው በሕይወቱ ሳለ መልካም ነገር ከማድረግና ደስ ከሚለው በቀር ሌላ የተሻለ ነገር እንደሌለ ተረድቼአለሁ።
መጽሐፈ መክብብ 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መክብብ 3:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች