2 ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-4

2 ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-4 አማ05

እንግዲህ ልጄ ሆይ! በኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጸጋ በርታ። በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የተማርከውን ትምህርት ሌሎችን ለማስተማር ችሎታ ላላቸውና ለታመኑ ሰዎች ዐደራ ስጥ። አንተም የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር በመሆን ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል። በወታደርነት የሚያገለግል ሰው የጦር አዛዡን ለማስደሰት ዝግጁ መሆን አለበት እንጂ ወታደራዊ ባልሆነ ጉዳይ ላይ አይውልም።