“ስለዚህም ለአገልጋዬ ለዳዊት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ አንተን የበግ መንጋ ከምትጠብቅበት መስክ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤ በሄድክበት ስፍራ ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ወደፊትም በተራመድህ መጠን ጠላቶችህን ድል አደረግሁልህ፤ ገና ደግሞ በዓለም እንደ ታወቁት ታላላቅ መሪዎች ዝነኛ አደርግሃለሁ። ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ አዘጋጅቴ በራሳቸው ቦታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መሳፍንትን ከሾምኩበት ጊዜ ጀምሮ ክፉ አድራጊዎች ቀድሞ ያደርጉት እንደ ነበረው አያስጨንቋቸውም፤ አንተንም ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከቤትህ አልጋህን የሚወርሱ ልጆች እተካልሃለሁ ብሎ ይገልጥልሃል። ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ። ለስሜ መጠሪያ ቤት የሚሠራልኝም እርሱ ነው፤ የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ። እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ስሕተት በሚፈጽምበትም ጊዜ አባት ልጁን እንደሚቀጣ እቀጣዋለሁ፤ ይሁን እንጂ በእርሱ ቦታ አንተ ትነግሥ ዘንድ ባስወገድኩት በሳኦል ላይ እንዳደረግሁ ዘለዓለማዊ ፍቅሬን ከልጅህ አላርቅም። ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ይጠነክራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 7:8-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች