የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መገደሉን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በድንጋጤ ተሸበረ፤ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት መኰንኖች ነበሩት፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የበኤሮት ተወላጆች የሆኑት የሪሞን ልጆች በዓናና ሬካብ ነበሩ፤ በኤሮት የብንያም ክፍል እንደ ሆነች ይታሰብ ነበር፤ የበኤሮት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎችም ወደ ጊታይም ተሰደው ከዚያን ዘመን ጀምሮ የሚኖሩት በዚያው ነበር።
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 4 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 4:1-3
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች