2 የጴጥሮስ መልእክት 2:1-2

2 የጴጥሮስ መልእክት 2:1-2 አማ05

ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። በዚህ ዐይነት ብዙዎች የእነርሱን አሳፋሪ መንገድ ይከተላሉ፤ ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል።