ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 18
18
ነቢዩ ሚክያስ ንጉሥ አክዓብን ማስጠንቀቁ
(1ነገ. 22፥1-28)
1የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በሀብት በበለጸገና ዝነኛ በሆነ ጊዜ የእርሱና የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቤተሰብ በጋብቻ እንዲተሳሰሩ አደረገ፤ 2ከጥቂት ዓመቶች በኋላም ኢዮሣፍጥ አክዓብን ለመጐብኘት ወደ ሰማርያ ከተማ ሄደ፤ አክዓብም ለኢዮሣፍጥና ለአጃቢዎቹ ክብር ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን ዐርዶ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ አክዓብ በገለዓድ በሚገኘው በራሞት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል ይተባበረው ዘንድ ኢዮሣፍጥን አግባባው፤ 3“በራሞት ላይ አደጋ ለመጣል ከእኔ ጋር ትዘምታለህን?” ሲል ጠየቀው።
ኢዮሣፍጥም “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱም እንተባበርሃለን አለው። 4ነገር ግን አስቀድመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ” አለው።
5ስለዚህ አክዓብ ቊጥራቸው አራት መቶ የሆነውን ነቢያት ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ ጦርነት ልክፈትን? ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው።
እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ እግዚአብሔርም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።
6ኢዮሣፍጥ ግን “በእርሱ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቅበት ሌላ ነቢይ በዚህ የለምን?” ሲል ጠየቀ።
7አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ ተብሎ የሚጠራ ሌላም ነቢይ አለ፤ ነገር ግን እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል ስለማይናገር እርሱን አልወደውም” ሲል መለሰለት።
ኢዮሣፍጥም “አንተ ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
8ከዚህ በኋላ ንጉሥ አክዓብ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች አንዱን ጠርቶ “ሚክያስን ፈልገህ በማግኘት በፍጥነት እንዲመጣ አድርግ” ሲል አዘዘው።
9በዚህ ጊዜ ሁለቱ ነገሥታት ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰው በሰማርያ ቅጽር በር አጠገብ በውጪ በኩል በሚገኘው አውድማ በየዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያቱም ሁሉ በነገሥታቱ ፊት ሆነው የትንቢት ቃል ይናገሩ ነበር፤ 10ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው። 11ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔር ድልን ይሰጥሃል” አሉት።
12ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስ “ሌሎች ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደ እነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው።
13ሚክያስ ግን “እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ የምናገር መሆኔን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።
14ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ፥ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት? ወይስ እንተው?” ሲል ጠየቀው።
ሚክያስም “ዝመትባት! በእርግጥም ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲል መለሰለት።
15አክዓብም “በእግዚአብሔር ስም ከእውነት በቀር እንዳትነግረኝ ብዬ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው።
16ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኰረብቶች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ’ ብሎአል” ሲል መለሰለት። #ዘኍ. 27፥17፤ ሕዝ. 34፥5፤ ማቴ. 9፥36፤ ማር. 6፥34።
17አክዓብም ኢዮሣፍጥን “እርሱ ዘወትር ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ብዬህ አልነበረምን?” አለው።
18ሚክያስም የሚናገረውን የትንቢት ቃል በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! እግዚአብሔር በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤ 19እግዚአብሔርም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማን ነው?’ ሲል ጠየቀ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ አቀረቡ፤ 20በመጨረሻ ግን አንድ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ‘እኔ ላሳስተው እችላለሁ’ አለ፤ እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው፤ 21መልአኩም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰ፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል’ አለው።”
22ሚክያስም “እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ በእነዚህ በነቢያትህ አንደበት የሐሰት መንፈስ እንዳስቀመጠ ታያለህን? ይህንንም ያደረገው በአንተ ላይ ጥፋትን ስለ ወሰነብህ ነው!” አለው።
23የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ መታውና “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
24ሚክያስም “ወደ ጓዳ ሄደህ በምትሸሸግበት ጊዜ ታገኘዋለህ” ሲል መለሰለት።
25በዚህን ጊዜ ንጉሥ አክዓብ ከጦር መኰንኖቹ አንዱን “ሚክያስን ያዘው፤ ወደ ከተማይቱ ገዢ ወደ አሞንና ወደ ልዑል ዮአሽ ውሰደው፤ 26እኔም ከዘመቻ በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
27ሚክያስም “አንተ ከዘመቻ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነው!” አለው። ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።
የአክዓብ መሞት
(1ነገ. 22፥29-35)
28ከዚህ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ወደ ራሞት ገለዓድ ወጡ፤ 29አክዓብም ኢዮሣፍጥን “ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ሌላ ልብስ እለብሳለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ።
30የሶርያ ንጉሥም “የእስራኤል ንጉሥ አክዓብን ነጥላችሁ ግደሉ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ። 31ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ስለ መሰላቸው በእርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከበቡት፤ ነገር ግን ኢዮሣፍጥ ጮኸ፤ እግዚአብሔር አምላክም ከእነርሱ እጅ በመታደግ አዳነው፤ እነርሱም በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተገቱ። 32የሠረገላዎቹ አዛዦች ኢዮሣፍጥ የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በተገነዘቡ ጊዜ እርሱን ማሳደድ ተዉ፤ 33ይሁን እንጂ አንድ የሶርያ ወታደር በአጋጣሚ ያስፈነጠረው ፍላጻ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል አልፎ አክዓብን መታው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን “እኔ ቈስያለሁ! ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ!” ሲል አዘዘው። 34ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ይታይ ነበር፤ ፀሐይ ስትጠልቅም ሞተ።
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 18: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997