አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 21:3-6

አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 21:3-6 አማ05

ታዲያ አሁን ምን ምግብ ትሰጠኛለህ? አምስት እንጀራ ወይም ያለህን ሌላ ነገር ስጠኝ።” ካህኑም “ከተቀደሰው ኅብስት በቀር ሕዝብ የሚመገበው እንጀራ የለኝም፤ ተከታዮችህ በቅርቡ ከሴቶች ጋር ሳይገናኙ ተቈጥበው በንጽሕና የቈዩ ከሆኑ፥ ይህን ኅብስት መብላት ይችላሉ” ሲል መለሰለት። ዳዊትም ለካህኑ መልሶ “ከብላቴኖቼ ጋር ወደ ተልእኮ በምሄድበት ጊዜ ሁሉ ከሴቶች እንርቃለን፤ ተራ ተልእኮ እንኳ በምናደርግበት ጊዜ ብላቴኖቼ ንጽሕናቸውን ይጠብቃሉ። ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?” ስለዚህም ካህኑ የተቀደሰውን ኅብስት አንሥቶ ለዳዊት ሰጠው፤ ካህኑ ያለው ምግብ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የቀረበው ኅብስት ብቻ ነበር፤ ይህም ኅብስት ከተቀደሰው ጠረጴዛ ላይ ተነሥቶ በሌላ አዲስ ኅብስት የተተካ ነበር።