1 የጴጥሮስ መልእክት 3:1-3

1 የጴጥሮስ መልእክት 3:1-3 አማ05

እንዲሁም እናንተ ሚስቶች! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዐይነት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ቃል የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃሉ ትምህርት በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል። ሊሳቡ የሚችሉትም ንጹሕ የሆነውንና ሰው አክባሪ የሆነውን ሕይወታችሁን ሲመለከቱ ነው። የእናንተ ውበት ጠጒርን በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና፥ የከበረ ልብስ በመልበስ በውጪ በሚታየው ጌጥ አይሁን።