አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 17
17
ናታን ለዳዊት የተናገረው ቃል
(2ሳሙ. 7፥1-17)
1ንጉሥ ዳዊት በዚህ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ነበር፤ አንድ ቀን ንጉሡ ነቢዩን ናታንን አስጠርቶ “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል!” አለው።
2ናታንም “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ በልብህ ያሰብከውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።
3ነገር ግን በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ናታንን እንዲህ አለው፤ 4“ወደ አገልጋዬ ወደ ዳዊት ሄደህ እንዲህ በለው ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤ 5የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት ነጻ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖሬ አላውቅም፤ ዘወትር በድንኳን ውስጥ ሆኜ ከቦታ ወደ ቦታ እዘዋወር ነበር፤ 6ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በተጓዝኩበት ዘመን ሁሉ እኔ ከሾምኳቸው መሪዎች መካከል አንዱን እንኳ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቤተ መቅደስ እንዲሠራልኝ የጠየቅሁት አለን?’
7“ስለዚህ እኔ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለአገልጋዬ ለዳዊት የምለውን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከበግ እረኝነት አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤ 8በሄድክበት ስፍራ ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ጠላቶችህን ሁሉ ድል አደረግኹልህ፤ በዓለም ላይ እንዳሉት እንደታላላቅ ዝነኞች ሰዎች ስምህን ዝነኛ አደርገዋለሁ። 9-10ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ እዚያም በገዛ ምድራቸው በሰላም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ ግፈኞች እንደ ቀድሞው በፍጹም አያስጨንቁአቸውም፤ ከዚህ በፊት በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን እንደ ሾምኩበት ጊዜ ያለ ችግር ዳግመኛ አይደርስባቸውም፤ ጠላቶችህን ሁሉ አስገዛልሃለሁ፤ እኔ እግዚአብሔርም ንጉሣዊ ቤትህን እንደምሠራልህ እገልጥልሃለሁ። 11ዕድሜህ ደርሶ ከአባቶችህ ጋር በሞት ስትቀላቀል፥ ከልጆችህ አንዱን አነግሣለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ። 12ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝም እርሱ ይሆናል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም የጸና እንዲሆን አደርጋለሁ፤ 13እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ አንተ በሳኦል እግር ተተክተህ ትነግሥ ዘንድ ከዙፋኑ ባወረድኩት በሳኦል ላይ ባደረግሁት ዐይነት ምሕረቴን ከልጅህ በማራቅ አልተወውም። #2ቆሮ. 6፥18፤ ዕብ. 1፥5። 14በሕዝቤና በመንግሥቴ ላይ ለዘለዓለም እሾመዋለሁ፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ አይኖረውም።’ ”
15በዚህ ዐይነት ናታን እግዚአብሔር የገለጠለትን ሁሉ ለዳዊት ነገረው።
ዳዊት ለእግዚአብሔር ያቀረበው የምስጋና ጸሎት
(2ሳሙ. 7፥18-29)
16ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን ሄደ፤ ተቀምጦም እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔ ይህን ሁሉ ነገር ታደርግልኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው? 17እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ያለፈው ሁሉ በፊትህ የማይበቃ ሆኖ ስለ አገልጋይህ ቤት ለሚመጣው ሩቅ ዘመን አሁንም እንደገና እኔን እንደ ትልቅ ባለማዕርግ አድርገህ ተመለከትከኝ። 18እንግዲህ ለአንተ ከዚህ በላይ ምን መናገር እችላለሁ? አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ይሁን እንጂ ለእኔ ክብር ሰጥተኸኛል፤ 19ይህን ታደርግልኝ ዘንድ እንዲሁም ወደፊት ታላቅ እንደምታደርገኝ ታስታውቀኝ ዘንድ በጎ ፈቃድህና ዕቅድህ ሆኖአል፤ 20እግዚአብሔር ሆይ ከቶ አንተን የሚመስል ማንም የለም፤ እንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም። 21ሕዝብህ እስራኤል ከየትኛው ሕዝብ ጋር ይነጻጸራል? አንተ እግዚአብሔር ከባርነት ነጻ አውጥተህ የራስህ ሕዝብ ያደረግኸው በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን? ሕዝብን ከግብጽ ለማስወጣት በመታደግህና በታላላቅ ሥራዎችህ ስምህን ታላቅና ገናና አደረግኸው። 22እስራኤልን ዘለዓለም የራስህ ሕዝብ አደረግህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተም አምላካቸው ሆንክ።
23“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ፈጽም፤ አደርጋለሁ ያልከውንም ሁሉ አድርግ፤ 24ይህንንም የምታደርገው ስምህ ለዘለዓለም የገነነ ይሆን ዘንድና ሰዎችም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው እንዲሉ ነው፤ የእኔ የአገልጋይህ ቤትም በፊትህ የጸና ይሆናል። 25አምላኬ ሆይ፥ አንተ ለእኔ ለባሪያህ ቤትን እንደምትሠራልኝ ስለ ገለጥክልኝ ይህን ጸሎት ለማቅረብ ድፍረት አገኘሁ። 26እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ አምላክ ነህ፤ ይህንንም አስደናቂ የተስፋ ቃል ለእኔ ሰጥተኸኛል፤ 27ስለዚህ በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የእኔን የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ቤተሰቤን ባርከኸዋል፤ እርሱም ለዘለዓለም የተባረከ ይሆናል።”
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 17: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997