ዘካርያስ 4:8-10

ዘካርያስ 4:8-10 NASV

ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣሉ፤ የሚፈጽሙትም የርሱ እጆች ናቸው። ከዚያም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። “የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱ በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”