መክብብ 1:2-8

መክብብ 1:2-8 NASV

“የከንቱ ከንቱ፤” ይላል ሰባኪው፤ “ሁሉም ነገር ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው።” ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል? ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። ፀሓይ ትወጣለች፤ ትጠልቃለችም፤ ወደምትወጣበትም ለመመለስ ትጣደፋለች። ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ይመለሳል፤ ዞሮ ዞሮ ይሄዳል፤ ዘወትርም ወደ ዑደቱ ይመለሳል። ወንዞች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ባሕሩ ግን ፈጽሞ አይሞላም፤ ወንዞች ወደ መጡበት ስፍራ፣ ወደዚያ እንደ ገና ይመለሳሉ። ሰው መናገር ከሚችለው በላይ፣ ነገሮች ሁሉ አድካሚ ናቸው፤ ዐይን ከማየት አይጠግብም፤ ጆሮም በመስማት አይሞላም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}